ኮልፌ ደንብ ማስከበር ጥር 30/2017 ዓ.ም
ፅህፈት ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ ስድስት ወራት የተከለሰ እቅድ ዙሪያ የዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች፣የደንብ ማስከበሪ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ባለድርሻ አካላት፣የክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም ከ11ዱ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የአይማኖት አባቶች በተገኙበት ውይይት አካሒዷል።
የክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙልጌታ ጎንፋ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት በተጠናቀቀው 6ወራት የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት የደንብ ጥሰቶችና ሕገ ወጥነትን የመከላከል ተግባራት ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
አቶ ሙልጌታ ጨምረውም ህገወጥነትን ከመከላከል ባሻገር ተቋሙን ሪፎርም በማድረግ በጠንካራ የሰው ሀይል የማደራጀት ፣ ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ተሳትፎ ማድረግ መቻሉን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም አገልግሎቶችን በማዘመን ተግባራትን በድልና በውጤታማነት ለመፈፀም ተግቶ መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ሀላፊው ጨምረውም በክፍለ ከተማው በህገ ወጥ የመሬት ወረራ፣ህገወጥ ንግድ ፣ህገወጥ እርድና ፣ህገወጥ የውጪ ማስታወቂያ፣በሌሎችም የደንብ ጥሰቶች እንዳይኖሩ ከፍተኛ ስራ መስራቱን ገልፀዋል።
አቶ ዱጉማ ዲባባ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አማካሪ በበኩላቸው የህዝብና የመንግስት ሀብት የሆነውን መሬትን በአግባቡ ያስጠበቀ ተቋም መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን እንዳይከሰቱ በመስራት የበለጠ ውጤታማ መሆን ይገባዋል ብለዋል።